Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ባሳዩት የዳኝነት ብቃት አድናቆት አገኙ

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን ስታሸንፍ ጨዋታዉን በመሀል ዳኝነት የመሩት ዳኛ ባምላክ ተሰማ ጨዋታዉን ለመምራት ባሳዩት ብቃት በአፍሪካ ዋንጫ ተመልካቾች እየተወደሱ ይገኛሉ፡፡
ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ከሰጡ በኋላ በተንቀሳቃሽ ምስል (VAR) በመታገዝ ዉሳኔዉ ትክክል ባለመሆኑ ሁለቱንም ቅጣት ምቶች የሻሩበት መንገድ ከብዙዎቹ የእግር ኳስ ተመልካቾች አድናቆትን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል፡፡
በመጀመሪያ የቡርኪናፋሶው ግብ ጠባቂ ሄርቬ ኮፊ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ከሴኔጋል አማካዩ ቼኩ ኩያቴ ጋር መጋጨቱን ተከትሎ ፔናሊቲ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ፥ የእለቱ ዋና ደኛ ባምላክ ተሰማ በተንቀሳቃሽ ምስል በታገዘ ዳኝነት(VAR) ፍፁም ቅጣት ምቱን በመሻር ጨዋታዉን በመልስ ምት አስቀጥለዋል።
ከጨዋታው የእረፍት ሰዓት መጠናቀቂ ቀደም ብሎ ኤድመንድ ታፕሶባ ኳስ በእጁ ነክቷል በሚል የእለቱ ዋና ዳኛ ለተጫዋቹ የቢጫ ካርድ ካሳዩት በኋላ በተንቀሳቃሽ ምስል በማረጋገጥ ዉሳኔዉ ልክ ባለመሆኑ ተጫዋቹ ያየዉን ቢጫ ካርድ አንስተዋል፡፡
በአጠቃላይ ውጥረት በበዛበት የቡርኪናፋሶ እና ሴኔጋል የፍፃሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ያሳዩት የዳኝነት ብቃት የእንግሊዝ ፕሪሜሪሊግ ዳኞችን ጨምሮ የሌሎችም ታላላቅ ሊግ ዳኞች ከኢትዮጵያዊዉ ዳኛ መማር አለባቸዉ ሲል ሜይል ኦንላይን በዘገባዉ አሰነብቧል፡፡
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካፍ ኢንተርናሽናል ዳኛዉን ባወደሰበት ፅሁፉ ፍፁም ጨዋ ፣ ዉሳኔዎቹ ላይ ፈጣን፣የሚመች የዳኝነት ስልት ያለዉ ሲል ገልፆታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.