Fana: At a Speed of Life!

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመስኖ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል – የሶማሌ ክልል መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሀላፊ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በመስኖ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ሲሉ የሶማሌ ክልል መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፊታህ መሀመድ ገለጸ፡፡

የመስኖ ልማት ሥራን በአግባቡ በመስራት እንደሀገር አሁን ያለውን ፈተና ፈጥኖ መውጣት እና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ለነገ የማይበል ሥራ ነው ብለዋል፡፡

የሶማሌ ክልል መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በሲቲ ዞን በኩላንና ሀራዎ ቀበሌዎች ለመስኖ ልማት የሚሆን ፕሮጀክት ግንባታና ጥገና ለማከናወን በድሬዳዋ ከተማ የምክክር መድረክ ማካሄዱን ከሶማሌ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የመስኖ ልማት እንቅስቃሴን ከግብ ለማድረስ በብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በሁሉም ዞኖች ጥገና ተደርጎ ስራ የጀመሩ መኖራቸውን የቢሮ ሀላፊው ተናግረዋል፡፡

አርሶ አደሩ የመስኖ ውሃን ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የሁሉም አካላት ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው፥ የሚመለከታቸው የመምሪያ ኃላፊዎች በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ህይወት ለመቀየር የግብርና ኢኮኖሚ ማዘመን ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ ዘይነብ ሀጅ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.