Fana: At a Speed of Life!

በቻይና ውሃን ግዛት ተጨማሪ 19 ጊዜያዊ ሆስፒታሎች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮረና ቫይረስ መነሻ በሆነችው ውሃን በወረርሽኙ የተጠቁ በሽተኞችን ለመቀበል 19 ጊዜያዊ ሆስፒታሎችን ለመገንባት ማቀዷን ቻይና ገለፀች።

ጊዜያዊ ሆስፒታሎቹ ሲጠናቀቁ እስከ 30 ሺህ አልጋዎችን የመያዝ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።

ውሃን እስካሁን ድረስ 13 ሺህ 348 አልጋዎች ያሉት 13 ቦታዎችን ወደ ጊዜያዊ ሆስፒታልነት የለወጠች ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ 9 ሺህ 313 አልጋዎች ቀላል ህመም ያለባቸውን ህመምተኞች ለማከም የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

ጊዜያዊ ሆስፒታሎቹ የህክምና አቅማቸውን ለማሻሻል እያንዳንዱ ሆስፒታል በሲቲ ስካነር፣ የታካሚዎችን የልብ ምት እና ሌሎች የልብ ችግሮች ለመተንተን የሚያገለግል መሣሪያ ጨምሮ በሌሎች የህክምና መሳሪያዎች ይደራጃሉም ነው የተባለው።

ወረርሽኙን ተከትሎ በከተማዋ የአልጋ እጥረትን ለመቅረፍ አንድ ፋብሪካን ጨምሮ የጂምናስቲክ፣ የስብሰባ እና የኤግዚቢሽን ማዕከላት ወደ ጊዜያዊ ሆስፒታልነት መቀየራቸው ተነግሯል።

ከእነዚህን አነስተኛ ሆስፒታሎች ሀሙስ እለት ግንባታው የተጠናቀቀው ሪሃኒ ሆስፒታል 3 ሺህ 690 አልጋዎች መያዙ ተገልጿል።

54 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ሆስፒታሉ አየር ማቀዝቀዣ፣ የመታጠቢያ ቤት ክፍሎች፣ ተንቀሳቃሽ መጸዳጃ ቤቶች፣ ቤተመፃህፍት፣ የፊልም መመልከቻ ስፍራዎች፣ ሬስቶራንቶቻና የመዝናኛ ሥፍራዎችን ያሟላ ነው።

ህመምተኞችን ለማከምና የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ከተለያዩ የቻይና ክልሎች 72 የሚሆኑ የህክምና ቡድኖች ወደ እነዚህ ጊዚያዊ ሆስፒታሎች መሰማራታቸው ተገልጿል።

ከመላው ቻይና በአጠቃላይ 32 ሺህ 572 የህክምና ባለሙያዎች የወረርስኙን ተጠቂዎች ለመታደግ ወደ ስፍራው መሰማራታቸው ተገልጿል።

 

ምንጭ፦ ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.