Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት በንጹሃን ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ሊያወግዝና ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪው ህወሓት አሁንም በንጹሃን ዜጎች እና በኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት እንዲወግዝ እና ተጠያቂ እንዲያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠይቀዋል።
 
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር፣ ከስዊድን እና አየርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በሰሜኑ የአገራችን ክፍል የተፈጠረውን ግጭት ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን የገለጹት አቶ ደመቀ÷ ይሁን እንጂ አሸባሪው ህወሓት በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚያደርገውን ዳግም ወረራ አጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያስረዱት፡፡
 
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም በጉዳዩ ላይ ዝምታውን በመስበር አሸባሪው ህወሓት በንጹሃን ዜጎች እና በኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት እንዲወግዝ እና ተጠያቂ እንዲያደርግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠይቀዋል፡፡
 
የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ ለትምህርት እና ለግብርናው ዘርፍ እንዲሁም ለሰብዓዊ እርዳታ የሚውል አዲስ የ80 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱ ተገልጿል፡፡
 
አቶ ደመቀ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ስቬንጃ ስቹልዚ ጋር ባደረጉት ውይይት÷ በሁለቱ አገራት መካከል ባለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡፡
 
አቶ ደመቀ የጀርመን መንግስት እና ህዝብ ለኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ከስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ከአየርላንድ የውጭ ጉዳይና መከላከያ ሚኒስትር ጋር በሁለትዮሽ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.