Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ የተላከ ልዩ ልኡክ ከግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ጋር ተገናኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተላከ ልዩ ልኡክ ከግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ ጋር ተገናኘ።

በልኡካን ቡድኑ ውስጥ የተካተቱት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁንና በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ናቸው፡፡

አቶ ኃይለማርያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተላከንም መልዕክት ለፕሬዚዳንት ኤል ሲሲ አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ልዑኩ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በነበረው ቆየታው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ተወያይቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.