አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዓለም የ10 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን ሰበረች
አዲ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፔን በተካሄደ የአለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው የዓለም የ10 ኪሎ ሜትር ክብረ ወሰንን በመስበር ጭምር ውድድሩን በበላይነት አጠናቀቀች፡፡
ከዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ አትሌት ያለምዘርፍ የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫን 29:14 በሆነ ጊዜ በመግባት ነው የዓለም ክብረወሰንን የሰበረችው፡፡
አትሌቷ ባለፈው የፈረንጆቹ ጥር ወር በቫሌንሺያ በተካሄደ ውድድር በርቀቱ ክብረወን የመስበር እቅድ የነበራት ቢሆንም የኮቪድ ምርመራ ውጤቷ ፓዘቲቭ በመሆኑ ሳትወዳደር ቀርታለች።
በሚቀጥሉት ወራት በግማሽ ማራቶን ውድድር የመሳተፍ እቅድ እንዳላትም ከዛሬው ውድድር በኋላ ተናግራለች።