Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ዛሬ በዶሃ ተካሂዷል።

በምድብ 1 አስተጋጇ ኳታር፣ ኔዘርላንድስ፣ ሴኔጋል እና ኢኳዶር፤

በምድብ 2 ደግሞ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ኢራን እና የዌልስ/ስኮትላንድ ወይም ዩክሬን አሸናፊ፤

በምድብ 3 አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ፣ ፖላንድ እና ሳዑዲ አረቢያ፤

በምድብ 4 ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ቱኒዚያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች/አውስትራሊያ ወይም የፔሩ አሸናፊ፤

በምድብ 5 ስፔን፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና የኮስታሪካ ወይም ኒውዝላንድ አሸናፊ፤

በምድብ 6 ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ሞሮኮ እና ካናዳ፤

በምድብ 7 ፖርቹጋል፣ ዑራጋይ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጋና፤

በምድብ 8 ብራዚል፣ ስዊዘርላንድ፣ ሰርቢያ እና ካሜሩን፤

የመክፈቻ ጨዋታው በአስተናጋጇ ኳታር እና በደቡብ አሜሪካዋ ተወካይ ኢኳዶር መካከል የሚደረግ ይሆናል።

ከ2010 የደቡብ አፍሪካው የዓለም ዋንጫ አይረሴ ትዝታ በኋላ ጋና እና ዑራጋይ ዳግም ተገናኝተዋል።

በወቅቱ የዑራጋዩ አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ ጎል ሊሆን የሚችልን ኳስ በተጨማሪ ሰአት መጠናቀቂያ ላይ በእጁ ካስቀረ በኋላ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ የሱዋሬዝን ኳስ በእጅ መንካት ተከትሎ የተገኘውን የፍጹም ቅጣት ምት አሳሞሃ ጅያን ሳይጠቀምበት ቀርቶ ዑራጋይ በመለያ ፍጹም ቅጣት ምት ቀጣዩን ዙር መቀላቀሏ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.