Fana: At a Speed of Life!

ህጻን ልጅን የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ህጻን ልጅን የኩላሊት ታማሚ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ታማሚ በማስመሰልና የሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ገንዘብ ሲያሰባስቡ በመገኘታቸው ነው፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት 11 ግለሰቦች ሲሆኑ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት በ3 ክፍለ ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በጸጥታ አካላት ክትትል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በተደረገው የክትትል ስራ ለህገ-ወጥ ስራው የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶችን፣ ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ የሆኑ ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም 9 ሴትና 2 ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.