Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደረሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ሥር የሚንቀሳቀሰው የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የሰብዓዊ ዕርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች መቐለ ደረሱ።
የድጋፍ ስርጭቱ በዚህ ሳምንት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ እንደሚጀምርም የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።
እርዳታው ለ43 ሺህ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ለሚሹ እና በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ለሆኑ 24 ሺህ ህጻናትና እናቶች ተደራሽ ይሆናልም ነው ያለው።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፥ 50 ዕርዳታ የጫኑና ነዳጅ የያዙ ቦቴዎች በሰላም መቐለ ደርሰዋል።
ተሽከርካሪዎቹ ምግብ፣ ዓልሚ ምግቦችን እና ሌሎች ሕይወት አድን ቁሳቁሶችን የጫኑ ናቸው።
ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ እና የተለያየ ጥራጥሬ ሲሆን፥ 700 ሜትሪክ ቶኑ ደግሞ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ የጤና የንጽህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል።
ከዚህ በተጨማሪም 115 ሺህ ሊትር ነዳጅም ከሰብአዊ እርዳታው ጋር መቐለ ደርሷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.