Fana: At a Speed of Life!

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ክፍል ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ውድመት ደርሶበት የነበረው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከረጂ ድርጅቶ በተገኘ ድጋፍ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ክፍሉከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ።
የሆስፒታሉ ስራ አሰኪያጅ ዶክተር ሀይማኖት አየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ ሆስፒታሉ ከዚህ በፌት 8 የሚደርሱ የቀዶ ጥገና ማሽነሪዎች የነበሩት ቢሆንም ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የቀዶ ጥገና ክፍሉ አስፈላጊነት ላቅ ያለ መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጇ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 5 ሚሊየን እንዱሁም ዮ ኤስ ኤይድ ትራንስፎርም የተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባደረጉት ድጋፍ አሁን ላይ 7 ማሸነሪዎች የገጠማ ሰራቸው ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብለዋል።
አሁን ላይ ስራ የሚጀምረው የቀዶ ጥገና ክፍሉ ከዚህ በፌት አገልግሎት ይሰጥበት ከነበረው በተሻለ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ በመልሶ ግንባታ ሂደቱ በተሻለ መንገድ እየተገነባ ነው ያሉት ስራ አስኪያጇ የተገልጋዮች ማረፊያ ግንባታም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በመልሶ ግንባታ ሂደቱ ረጂ ድርጅቶች እና ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት ስራ አስኪያጇ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.