በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች የኢትዮጵያ ማዕድን ጋለሪን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያየ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ባለሀብቶች በማዕድን ሚኒስቴር የተገነባውን የኢትዮጵያ ማዕድን ጋለሪን መጎብኘታቸውን ሚኒስቴሩ አስታወቀ።
የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት÷ የማዕድን ጋለሪው የኢትዮጵያን የማዕድን ሀብት መረጃን በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ የያዘ፣ ለምርምር የሚረዳና በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች ዋና ግብአት መሆን የሚችል ነው።
ባለሀብቶቹ በማዕድን ሚኒስቴር የተገነባውን የኢትዮጵያ ማዕድን ጋለሪና የተቋሙን የለውጥ ስራዎችንም ነው የጎበኙት፡፡