Fana: At a Speed of Life!

በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች።

ዛሬ በተካሄዱ ውድድሮች በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች ኢትዮጵያ የወርቅና የብር ሜዳልያ አግኝታለች።

በውድድሩ አትሌት ወርቁውሃ ጌታቸው እና ዘርፌ ወንድማገኝ አንደኛ እና ሁለተኛ በመውጣት የወርቅና የብር ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ አትሌት ኃ/ማርያም አማረ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አምጥቷል፡፡

ረፋድ ላይ በተካሄደ የ20 ኪሎ ሜትር እርምጃ ውድድርም በሁለቱም ጾታዎች ተጨማሪ ሜዳልያ ማግኘት ተችሏል።

በዚህም በሴቶች አትሌት የኋልዬ በለጠው ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳልያ አስገኝታለች።

በወንዶቹ ደግሞ ዮሐንስ አልጋው ሦስተኛ በመውጣት የነሃስ ሜዳልያ ማስገኘቱን የአትሌቲክ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.