የመከላከያ ሰራዊቱን ወታደራዊ ዝግጁነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም ለማሳደግ እና ወደ ላቀ ወታደራዊ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ለማድረስ የመከላከያ ክፍሎች የታለመውን ዕቅድ መነሻ አድርገው ግቡን ማሳካታቸውን የመከላከያ ኢንስፔክተር ጀኔራል ቢሮ አስታወቀ፡፡
የመከላከያ ኢንስፔክተር ጀኔራል ቢሮ ኃላፊ ሌተናንት ጄነራል ድሪባ መኮንን÷ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ መሰናክሎችን ጥሶ በማለፍ ግዳጅ መፈፀም የሚችል ቁመና መገንባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊት ሀገርን ለማፍረስ የሚመጣን ወራሪ እና ፀረ ሰላም ኃይል መደምሰስ እንደሚችል ታልሞ የተቀረፀ መሆኑን ገልጸው÷ ይህንኑ እውነታ በስልጠና ብቃት፣ በስነ አእምሮ ጥንካሬ እና በሁለንተናዊው የቁሳቁስ ዝግጁነት አስተማማኝ በሆነ አግባብ ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡
በኢንስፔክሽን ደረጃ ሰራዊታችን ያካሄደውን ውጊያ ማዕከል አድርጎ ለቀጣይ ስራ እንዴት መዘጋጀት እንዳለበት አቅጣጫ የሰጠ እና ግንዛቤ የፈጠረ ስልጠና መሰጡትን ጠቁመው÷ የክፍሉ አባላትም በሁሉም የመከላከያ ክፍሎች በመሰማራት የሰራዊታችንን ወቅታዊ አጠቃላይ የዝግጁነት ደራጃ ማረጋገጥ ችለዋል ማለታቸውን ከለመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!