በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኦሬገን በሚካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክለው የአትሌቲክስ ቡድን በዛሬው ዕለት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት÷ ዛሬ ምሽት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ለቡድኑ መልካም እድል ተመኝተው ሸኝተዋል፡፡
18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻ ምፒዮና በአሜሪካ ኦሬገን ከሐምሌ 14 ቀን እስከ 25 ቀን 2022 እንደሚካሄድ ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡