በ2015 ዓ.ም. ከወጪ ንግድ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዷል- የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀጣይ በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማምጣት መታቀዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
ዛሬ እየተከበረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ቀን አስመልክቶ “የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ምርት ይግዙ” በሚል መሪ ሐሳብ አውደ ርዕይ ተከፍቷል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በአውደ ርዕዩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በ2015 ዓ.ም ከወጪ ንግድ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመው÷ በቀጣዮቹ ዓመታት ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ 10 ቢሊየን ዶላር እንዲሆን እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ÷ 60 ላኪዎች እና ሦስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡
በአውደ ርዕዩ ላይ የተሳተፉ 12 ዘርፎች÷ ምርት ወደ ውጪ በመላክ ከ25 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘታቸው ተገልጿል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 1 ቢሊየን ዶላር የተገኘ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ ደግሞ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላሩ ከቡና የተገኘ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በዘቢብ ተክላይ እና በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!