Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን 35 የታጠቁ የሽፍታ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ወምበራ ወረዳ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተወጣጡ 35 የታጠቁ የሽፍታ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸው ተገለጸ፡፡

የቡድኑ አባላት በቀጠናው እየተካሄደ ካለው ሕግ ማስከበር ተግባር ጋር ተያይዞ  የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ነው እጃቸውን የሰጡት፡፡

እጅ ከሰጡት መካከል 12ቱ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸውን የመተከል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የወምበራ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገመዳ ዱጋዝ÷የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል የቡድኑ አባላት ለመንግስት እጅ መስጠታቸው ለሰላም ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት ያሳያል ብለዋል።

በወረዳው ኮማንድ ፖስት ከፍተኛ አመራር ኮለኔል አሰፋ አየለ በበኩላቸው÷የጉሙዝ ማህበረሰብ ባለፉት ሶስት አመታት በጸረ ሰላም ሃይሎች ከቀየው ሲታፈንና ሲሰቃይ መቆየቱን አስታውሰው÷ይሄንን እኩይ ተግባር በጋራ መታገል ይገባል ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.