Fana: At a Speed of Life!

ዋልያዎቹ በቻን ማጣሪያ የደቡብ ሱዳን አቻቸውን 5 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ እግር ኳስ ሻምፒዮና (ቻን) ጨዋታ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያደረገውን የመልስ ጨዋታ 5 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ።
 
ሰባተኛው የቻን የእግር ኳስ ጨዋታበፈረንጆቹ 2023 በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
 
ዋልያዎቹ ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ባደረጉት የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታያለ ምንም ግብ አቻ ቢለያዩም በመልሱ ጨዋታ 5 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
 
በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን ባደረገው የመልስ ጨዋታ በረመዳን የሱፍ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ መስዑድ መሐመድ፣ ይገዙ ቦጋለ እና ፒተር ሜከር (በራሱ ግብ ላይ) ባስቆጠሩት ግብ ዋሊያዎቹ አሸንፈው ወጥተዋል።
 
ዋልያዎቹ ወደ ውድድሩ ለማለፍ ከሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጨረሻ የማጣሪያ ጨዋታቸውን በፈረንጆቹ 2022 ነሐሴ ላይ ያደርጋሉ።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.