Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ÷ የአስፈጻሚ አካላት የአፈጻጸም ሪፖርት፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር ሪፖርቶችን እንዲሁም የክልሉን መንግሥት የ2015 ዓመት የሥራ ዕቅድ፣ ረቂቅ በጀት እና ሌሎች አዋጆችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

በጉባኤው ዋና አፈ ጉባኤ ወንድሙ ኩርታ÷ ክልላዊ አንድነትን የማጠናከር ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል ።

በክልሉ መሪን ከመሪ፣ ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ስሜት ቀስቃሽ መልዕክቶችን የሚያሰራጩ እና አላስፈላጊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላትን ማውገዝ እንደሚገባም ገልጸዋል ።

በክልሉ ያልተፈቱ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን በመንግስት አሰራር መሰረት እንዲፈቱ የማድረግ ስራ መሰራቱን በመጥቀስም፥ ክልላዊ አንድነትን የማጠናከር ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ዋና አፈ ጉባዔዉ አመላክተዋል።

ክልሉ ከተመሰረተ በአጭር ወራት የተለያዩ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ስራ በመግባት አኩሪ ተግባራት መፈጸሙን ተናግረው በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና የመንግስት አሰራር ፣የህዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥባቸው በመሆናቸው ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ጉባዔው በሁለት ቀናት ቆይታው÷ ሹመቶችንም እንደሚያፀድቅ ተመላክቷል፡፡

በበርናባስ ተስፋዬ ተጨማሪ መረጃ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.