Fana: At a Speed of Life!

ከቀረጥ ነጻ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች መሸጫ ሱቅ በይፋ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከቀረጥ ነጻ የቆዳና ቆዳ ውጤቶች መሸጫ ሱቅ በይፋ ከፍቶ አስመርቋል፡፡
 
የመሸጫ ሱቁ የኢትዮጵያን ምርቶች ማስተዋወቅና የዘርፉን ወጪ ንግድ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
የኢንዱትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በመክፈቻ መርሐ ግብሩ ላይ እንደገለጹት ÷ በዘርፉ ሁለንተናዊ ዕድገት ለማምጣት ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው፡፡
 
የወጪ ንግድ ገቢን፣ የማምረት አቅም አጠቃቃምን በማሳደግ እና የገጽታ ግንባት ሥራ በመሥራት በኩል እንደ ሀገር ለተጀመረው “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ መሳካት የፕሮጀክቱ እውን መሆን አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
 
መሰል ፕሮጀክቶች ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማዳበር እና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡
 
በቀረጥ ነጻ የቆዳ ውጤቶች የሽያጭ ማዕከል የተሳተፉ ሥምንት ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለዕይታና ሽያጭ ማቅረባቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የጃፓን ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ጃይካ) የኤክስፖርት ማስተዋወቅ ፕሮጀክት ዋና አማካሪ ኖሪክ ናጋይ÷ድርጅታቸው የኢትዮጵያን ቆዳና ቆዳ ውጤቶች ለዓለም ገበያ በማስተዋወቅ ዕውቅና እንዲያገኝ ለማድርግ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.