Fana: At a Speed of Life!

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር መንስዔ እና ህክምናው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ካንሰር ከሰውነታችን ቁጥጥር ውጪ የሆነ የህዋሳት መብዛት ሲኖር የሚከሰት በሽታ መሆኑ ይነገራል፡፡

የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰር በሽታ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ ኤች ፒ ቪ በተባለ እና የሴቶችን መራቢያ አካል ፣ ማህፀን እንዲሁም የማህፀን በርን በሚያጠቃ ቫይረስ የሚመጣ መሆኑን የማህፀን እና ፅንስ ሃኪም ዶክተር እንዳለ ይገዙ ይናገራሉ፡፡

እንደ ዶክተር ይናገር ገለፃ ይህ ቫይረስ በግንኙነት ጊዜ የሚተላለፍ ሲሆን ከአንድ በላይ የፍቅር አጋር መኖር (ከአንድ በላይ የወሲብ ጓደኛ መኖር) ደግሞ ለዚህ ቫይረስ መተላለፍ ያጋልጣል፡፡

የማሕፀን በር ጫፍ ካንሰር ምልክቶችን በተመለከተ በሽታው ብዙ ጊዜ ምልክት ሳያሳይ ሊቆይ እንደሚችልም ነው የሚናገሩት።

በሂደት የቅድመ ካንሰር ምልክቶችን ማሳየት ይጀምርና በመቀጠል ወደ ካንሰርነት ይቀየራል ነው ያሉት፡፡

ለበሽታው የሚሰጥን ክትባት መውሰድ ደግሞ ለመከላከል እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር እንደየደረጃው ህክምናውም እንደሚለያይ የተናገሩት የህክምና ባለሙያው በአጠቃላይ ግን የሚሰጡት ህክምናዎች የቀዶ ጥገና ህክምና፣ የጨረር ህክምና የኬሞ ቴራፒ ህክምና መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባወጣው መረጃ መሰረት በየዓመቱ ከ7 ሺህ በላይ ሴቶች የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ይታይባቸዋል፡፡

ከእነዚህ ውስጥ 5 ሺህ የሚሆኑት በበሽታው ምክንያት ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.