Fana: At a Speed of Life!

መንግስት የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡትን ሪፖርት ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 11 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች ኢትዮጵያን በተመለከተ ያወጡት ሪፖርት የፖለቲካ አጀንዳ ለመፍጠር ታልሞ የተሰራ ነው ሲል ውድቅ አድርጎታል።

ቡድኑ ላለፉት 10 ወራት በኢትዮጵያ ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከዓለም አቀፍ ህግ እና ከስደተኛ ህጎች አንፃር አጣራለሁ ብሎ ሲሰራ ቆይቷል።

ይሁን እንጅ ከጅምሩ እንቅስቃሴው ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ተፈፀመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር የተቋቋመው የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ታደሰ ካሳ ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽኑ ይፋ ያደረገው ‘‘ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ ቁንፅል የሆነ ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መርሆዎች መሰረት ያላደረገ እና አባሪ ማስረጃዎች የሌሉት፣ የተፈፀሙ ሰብዓዊ መብቶችን ከማጣራት ይልቅ የፖለቲካ አቋምን ለማሳየት የወጣ ነው ብለዋል” ዶ/ር ታደሰ፡፡

በዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቡድን የቀረበው ሪፖርት በሶስቱም ክልሎች ደረሰ ከተባለውና ሁሉም ከሚያውቀው የጥፋት መጠንና አይነት አንፃር የሚመጣጠን አይደለም ሲሉም መንግስት ሪፖርቱን እንደማይቀበለው ተናግረዋል ፡፡

ሪፖርቱ በጣም ቁንፅል የሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው ያሉት ዶክተር ታደሰ÷ ስለሂደቶችም ሆነ ኮሚሽኑ የተከተለው የምርመራ ስራ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተቀመጡ መሰረታዊ እሳቤዎችን መሰረት በማድረግ የተዘጋጀ አይደለምም ነው ያሉት ፡፡

ከመረጃ አሰባሰብ ጋር በተያያዘም ብዙዎቹ የኮሚሽኑ ሪፖርት ምንጮችን የማይገልፁ፣ አንዳንዶችም ጥያቄ የሚነሳባቸው እና እንደምንጭ መጠቀሳቸው የምርመራ ቡድኑ ያዘጋጀው ሪፖርት በቅን ልቦና የተዘጋጀ ሳይሆን የተወሰኑ ኃይሎች ከጀርባ የሚያንቀሳቅሱትና የእነርሱን አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ነው ሲል መንግስት ያየዋል ብለዋል፡፡

በፀጋዬ ወንደሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.