Fana: At a Speed of Life!

ስደትን ለመከላከል ለወጣቶች አማራጭ የሥራ እድል መፍጠር እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕገወጥ የሰዎች ዝዉዉርና ስደትን ለመከላከል ለወጣቶች አማራጭ የሥራ እድል መፍጠር ተገቢ ነው ተባለ፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጂቶች በሀገር ዕድገት ላይ ያላቸዉን ሚና መጠቀም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“ቀለም ኢትዮጵያ” በ15 ሚሊየን ብር ያስገነባዉን የወጣቶች ሥራ-ተኮር የስልጠና ማዕከል በኮምቦልቻ ከተማ ሲያስመርቅ ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት፥ መንግስት ባልደረሰባቸዉ የማህበረሰብ የመልማት ፍላጎቶች ዉስጥ የሲቪል ድርጂቶች ክፍተቱን ለመሙላት የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ ነው፡፡

ቀለም ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር ባለበት ኮምቦልቻ ከተማ ያስገነባዉ ወጣት ተኮር የስልጠና ማዕከልም በግንባታ ፍጻሜ፣ በኤሌክትሮኒክስ፣ በብረት ሥራና ሌሎች በተመረጡ ዘርፎች አጫጭር ስልጠናዎችን ይሰጣል፡፡

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልአዚዝ ይመር፥ በአካባቢው ያለዉን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ከመነሻው ለማስቀረት ለወጣቶች አማራጭ የሥራ እድል መፍጠር ተገቢ በመሆኑ ይህንን መሰል ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ መለሰ በበኩላቸው፥ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ችግር-ፈቺ የሆኑ ሀሳቦችን በማህበረሰብ ውስጥ በመተግበር የመተጋገዝ ባህላችንን ማዳበር ይገባናል ብለዋል።

በኢሳያስ ገላው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.