Fana: At a Speed of Life!

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ 453 ተማሪዎችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በ25ኛ ዙር የምረቃ ስነስርዓቱ 453 የጤና ባለሙያዎችን አስመርቋል።

ከእነዚህ መካከል 175 የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ የተቀሩት በሌሎች የጤና እና ህክምና ሳይንስ የሠለጠኑ መሆናቸው ተገልጿል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 26 በመቶው ሴቶች ሲሆኑ ሁለት ሴት ተማሪዎች 3 ነጥብ 99 በማምጣት የሜዳሊያ ተሸላሚ መሆናቸው ታውቋል።

ለተመራቂዎች የስራ መመሪያ የሰጡት የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ምሩቃን በተማሩበት ዘርፍ በሃላፊነትና በቅንነት ማህበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኮሌጁ ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ 16 ሺህ 500 የጤና ባለሙያዎች ማፍራቱም ነው የተገለጸው።

በእነዚህ ዓመታት ቆይታውም ከ2 ሺህ በላይ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለማህበረሰቡ ማበርከቱም ታውቋል።

የዘንድሮ ተመራቂዎች ሐረሪና ሶማሌ ክልሎችን ጨምሮ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን1 ሚሊየን ብር የሚገመት ነፃ የህክምና አገልግሎት መስጠታቸውም ነው የተገለጸው።

የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጁ በአሁኑ ጊዜ በቅድመ ምረቃ 2 ሺህ 1 እነዲሁም በድህረ ምረቃ 1 ሺህ 79 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.