Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከሶማሊያ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ውድድር ከሶማሊያ አቻው ጋር ዛሬ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

በሴካፋ ዞን የማጣሪያ ውድድር በምድብ ሀ የተደለደለው የታዳጊዎች ብሔራዊ ቡድን 10 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

በምድብ ለ የተደለደሉት ዩጋንዳ እና ቡሩንዲ ቀደም ብለው ቀን 7 ሰዓት ላይ የመክፈቻ ጨዋታ የሚያደርጉ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.