Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ባለፉት 3 ወራት ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ከ886 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ሶስት ወራት ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ብቻ ከ886 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የከተማዋ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ዛሬ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት እንዳመላከተው ÷ ገቢው በጽህፈት ቤቱ አስተባባሪነት በዘጠኙ የተጠሪ ተቋማት አማካይነት ነው የተሰበሰበው፡፡
በዚህ መሠረትም ከውሃና ፍሳሽ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ከ501 ሚሊየን 626 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡
ከቄራዎች አገልግሎት ከ123 ሚሊየን 632 ሺህ ብር በላይ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን÷ ከከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት ደግሞ ከ196 ሚሊየን 998 ሺህ ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።
ከዚህ ባለፈም ከኤግዚቢሽን ማዕከል ከ57 ሚሊየን ብር በላይ፣ ከወሳኝ ኩነት ዘርፍ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ እንዲሁም ከአዲስ ዙ ፖርክ ከ2 ሚሊየን 456 ሺህ ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡
የገቢ አፈጻጸሙም በዕቅድ ከተያዘው ከመቶ ፐርሰንት በላይ እንደሆነ መገለጹን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ
ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.