Fana: At a Speed of Life!

የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን መክፈቻ ስነ-ስርዓት ነገ ይካሄዳል።

ሁለቱ ምክር ቤቶች ባለፈው 2014 ዓ.ም የ1ኛ ዓመት የስራ ዘመናቸውን አጠናቀው በ2015 ዓ.ም የ2ኛ ዓመት የስራ የዘመናቸው የሚይዙ ይሆናል፡፡

በዚህም 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ነገ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንቷ የመንግስት ዕቅድን በሚመለከት ለሁለቱ ምክር ቤቶች ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመርሃ ግብሩ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.