Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ለልማትና ፕላን ቋሚ ኮሚቴ መራ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ ክፍያ ማሻሻያ፣ የመንግስትና የግል አጋርነት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ ሌሎች የተወያየባቸውን አጀንዳዎች ለልማትና ፕላን ቋሚ ኮሚቴ መራ፡፡

ምክር ቤቱ በ2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መምሮ በሙሉ ድምፅ በማፅደቅ ለዝርዝር ዕይታ ለልማት እና ፕላን ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

በቅድሚያ ከጣሊያን መንግሥት የተገኘ ብድርን ለማጸደቅ የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1/2015 ሲሆን ረቂቅ አዋጁ በሙሉ ድምፅ ፀድቆ ለዝርዝር ዕይታ ለልማት እና ፕላን ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

ብሔራዋ የክፍያ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ዓለም የደረሰበትን የዲጂታል ስርአትን ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል የግልና የመንግስት አጋርነት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ የግል ዘርፉን የሚያበረታታና ያለውን አቅም ለመጠቀም የሚያስችል እንደሆነ ነው የተነሳው።

በረቂቅ አዋጆች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከምክር ቤቱ አባላት ተነስተዋል።

የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ሲደረግ በቂ ዝግጅት ስለመደረጉ፣ የዲጂታል ክፍያ ስርአትን የሚመጥን የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ስለመኖሩ፣ የፋይናንስ ደህንነት ቅድመ ዝግጅቶች ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል ይገኙበታል።

መንግስት ከውጭ ባለሐብቶች ይልቅ ለሀገር ውስጥ የግል አልሚዎች ማበረታቻዎችን እንዲያደርግ፣ ሁሉንም የህዝብ ፍላጎቶች በመንግስት ብቻ የማይሟሉ በመሆኑ ለግል ሴክተር ትኩረት መሰጠቱ በአወንታ እንደሚነሳም ነው የተገለፀው።

በተያያዘም ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ በምክር ቤቱ ቀርበው ያደረጉት ንግግር የድጋፍ ሞሽን ተደምጧል።

በርዕሰ ብሔሯ ንግግር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ ማብራሪያ እንደሚሰጡም ተጠቁሟል።

በአፈወርቅ እያዩና ምንይችል አዘዘው

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.