Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሲዳማ እና ሐረሪ ክልሎች የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ነገ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ሲዳማ እና ሐረሪ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ነገ ይካሄዳል፡፡

በኦሮሚያ እና ጋምቤላ ክልሎች ነገ የዓለም አቀፉን ያልተገባ ጣልቃ ገብነት እና ጫና የሚቃወም ህዝባዊ ሰልፍ ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን የክልሎቹ  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቀዋል፡፡

በተመሳሳይ   በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ ሲዳማ እና ሐረሪ  ክልሎች በነገው ዕለት የውጪ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሠልፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

በአማራ ክልልም የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም እና የኢትዮጵያን እውነት የሚደግፍ ሰልፍ የፊታችን ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡

ህዝባዊ ሰልፉ ”ለኢትዮጵያ እቆማለሁ ድምጼን አሰማለሁ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው፡፡

ሰልፉ በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ በውጭና በውስጥ ጠላቶች የሚደረግ የትኛውም አይነት ጫና እና ጣልቃ ገብነት ተቀባይነት እንደለሌው የክልሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን መቆሙን የሚገልፅበትና ለጠላት ምላሽ የሚሰጥበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የክልሎቹ ነዋሪዎችም በተደራጀ መልኩ በሰልፉ ላይ በመካፈል የምዕራባውያንን ጣልቃ ገብነት ከፍ ባለ ድምፅ ማውገዝና ለመንግስት ያላቸውን አጋርነት በነቂስ ወጥተው እንዲያሳዩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.