Fana: At a Speed of Life!

በስንዴ ልማት የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በማጠናከር በምግብ እራሳችንን መቻል አለብን – አቶ አወል አርባ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በስንዴ ልማት የጀመርነውን ስራ ይበልጥ በማጠናከር በምግብ እራሳችንን መቻል አለብን ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

አቶ አወል አርባ በአፋር ክልል የስንዴ እርሻ ልማት በሚከናወንባቸው ወረዳዎች ከሚገኙ አመራሮች እና በስንዴ እርሻ ከተሰማሩ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ አወል በውይይት መድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ የስንዴ እርሻ ልማት በሚካሄድባቸው አከባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለዘርፉ አስፈላጊውን ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡

በስንዴ እርሻ ልማት ላይ የጀመርነው ስራ ይበልጥ በማጠናከር በምግብ እራሳችንን መቻል አለብን ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ይህ እንቅስቃሴም ጠላቶቻችንን ተስፋ የሚያስቆርጥ ሲሆን÷ ለእኛ ደግሞ የእድገታችን አንድ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡
.
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለስንዴ እርሻ የተሰጠውን ትኩረት መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ ለማከናወን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝት ሊሰሩ እንዲሚገባ ተመላክቷል፡፡

አሁን ላይ የስንዴ እረሻን ከጀመሩ ወረዳዎች በተጨማሪ ልማቱን በሌሎች አካባቢዎች ለማስፋፋት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ መገለጹንም የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.