ለኮሮና ቫይረስ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል የስልክ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በኮሮና ቫይረስ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የ444 የስልክ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ ይፋ አደረገ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የገንዘብና ቁሳቁስ አቅርቦት ማሰባሰቢያ ብሄራዊ የድጋፍ ሰብሳቢ ኮሚቴ አቋቁመዋል።
በዚህ መሰረት ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ማሳተፍ የሚያስችል የገቢ ማሰባቢያውን ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
በመሆኑም ፡
ለ1 ብር A
ለ5 ብር B
ለ10 ብር C
ለ25 ብር D
ለ50 ብር E
ለ100 ብር F
ለ300 ብር G
ለ500 ብር H
ለ1000 ብር J
ወደ 444 በመላክ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል አስታውቋል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision