የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን እየገመገመ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሥራ አሥፈፃሚ አካላት የ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየገመገሙ ነው።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሥራዎችን መገምገም እና በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸውንም ለመለየት አፈጻጸምን በየወቅቱ መገምገም መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ፕሮጀክቶች እንደሚሠሩ ጠቁመው ተግባራቱ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ÷ አመራሩ ሥራዎቹን በአግባቡ መከተታልና ውጤታማነታቸውን በየጊዜው መገምገም እና ክፍተቶች ሲኖሩም ፈጥኖ ማረም አለበት ብለዋል፡፡
በግምገማው በክልሉ የሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን÷ በኢኮኖሚ ፣ በማኅበራዊ ፣ በመሠረተ ልማትና አስተዳደር እንዲሁም መልካም አስተዳደር ላይ የተሠሩ ሥራዎችን የዘርፉ አቅርበዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች እየተሳተፉ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!