Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች እየተካሄዱ ነው።

በውይይቶቹ የሠላም ስምምነቱን ተከትሎ የተገኙ ለውጦችና ውስንነቶች ላይ ምክክር ተደርጓል።

በአክሱምና አድዋ ከተሞች እየተደረጉ ባሉ ምክክሮች የፌደራል መንግስቱ ወደ ከተሞች ከገባ በኋላ ሠላምና ፀጥታ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት፣ የመሠረተ ልማት ሥራዎች እንዲሁም  ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በምክክሩ ጦርነት አስከፊ በመሆኑ ያለፉ ችግሮች መደገም እንደሌለባቸው የተነሳ ሲሆን ሠላም የትግራይ ሕዝብ ቀዳሚ ምርጫ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተመሳሳይ ሥነ-ልቦናዊ ዕሳቤና ፍላጎት መኖሩ እንዲሁም የመሰረተ ልማትና አስተዳደር ይቋቋምልን የሚሉ ሀሳቦች መነሳታቸውም ተገልጿል፡፡

በመሠረተ ልማት ላይ ስርቆት እየተፈጸመ የአገልግሎት መስተጓጎል በመፈጠሩ ትኩረት እንዲያገኝ ኅብረተሰቡ ጠይቋል።

የሰብዓዊ አቅርቦቶች እንዲጠናከሩም ተወያዮቹ ጠይቀዋል።

የሠላም ስምምነቱ ከተሞቹን ወደ ቀደመ ሁኔታቸው ለመመለስና ለማልማት ተሥፋ የሰነቀ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

ሠላም የሕዝብ ምርጫ መሆኑን በመጥቀስም፥ ለዘላቂ ሠላም መረጋገጥ ሁሉም ባለድርሻ አወንታዊ ሚና ሊጫወት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.