Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት የውጪ ምንዛሪ ድጋፍ የቀረበ 30 ነጥብ 3 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት ለማህበረሰቡ እየተሰራጨ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
ሚኒስቴሩ መጪውን የገና እና የጥምቀት በዓላት አስመልክቶ ከሚፈጠር ሰው ሰራሽ የአቅርቦት እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ሕብረተሰቡን ለመታደግ የቅድመ ዝግጅት እቅድ አውጥቶ በተዋረድ ካለው መዋቅርና ከባለድርሻዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡
 
በዚህ መሰረትም የቅድመ ዝግት እቅድ አፈፃጸሙንም በዛሬው ዕለት ከአምራቾች፣ ከአቅራቢዎችና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር ገምግሟል፡፡
 
በመድረኩም በአሁኑ ወቅት 30 ሚሊየን 340 ሺ 667 ሊትር የምግብ ዘይት የትግራይ ክልልን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል እየተሰራጭ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
 
በቅድመ ዝግጀት እቅዱ በተሰራ የንቅናቄ ስራ በሀገር ውስጥ በቂ ምርት የቀረበ በመሆኑ ለመጪዎቹ በዓላት ምንም አይነት የምግብ ዘይት እጥረት እንደማየገጥም መረጋገጡንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.