Fana: At a Speed of Life!

የሚሲዮን መሪዎች የመከላከያ ሚኒስቴርን ሪፎርም የሚያግዝ ተግባር ማከናወን አለባቸው – ዶ/ር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች በመከላከያ ሚኒስቴር እየተተገበረ ያለውን ማሻሻያ የሚያጠናክር ስራ መስራት እንዳለባቸው የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ ተናግረዋል።
 
ሚኒስትሩ ሱሉልታ በሚገኘው የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ በመገኘት ለውጭ ጉዳይ የስራ ሃላፊዎች እና ለሚሲዮን መሪዎች በተቋሙ እየተተገበረ ስላለው የሪፎርም ስራ ገለጻ አድርገዋል።
 
ኢትዮጵያን ወክለው ወደ ተለያዩ ሀገራት የሚሄዱ አምባሳደሮች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ በአካል፣ በእውቀት፣ በትጥቅ፣ በመረጃና በቴክኖሎጂ የላቀ እንዲሆን አስፈላጊውን እገዛ እንዲደረግ ብርቱ ስራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
 
መድረኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን÷ገለጻውን መነሻ በማድረግ ምክክር መደረጉንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.