Fana: At a Speed of Life!

በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት ለተመዘገቡ የጤና ባለሙያዎች የቀጥታ ኢንተርኔት ስልጠና ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመሰማራት ለሚልጉ የጤና ባለሙያዎች ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

ሚኒስቴሩ ያወጣውን ጥሪ ተከትሎ የጤና ባለሙያዎች በድረ ገፅ ተመዝገበዋል።

በመሆኑም ባለሙያዎችን ወደ ስራ ለማሰማራት በቅድሚያ ከስራው ጋር የተያያዘ እውቀት፣ ክህሎት ብሎም አመለካከትን ለማሳደግ የቀጥታ (ኦንላይን) ስልጠና እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

የጤና ባለሙያዎቹም ስልጠናውን እንዳጠናቀቁ የሚገልፀውን ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በቀጣይ ለሚኖረው ተግባር ስለሚፈለግ ፕሪንት በማድረግ እንዲወስዱ አሳስቧል።

ስለዚህ የቀጥታ ስልጠናውን ለመውሰድ የሚከተለውን አድራሻ (ሊንክ) www.moh.gov.et/covid19-courses/ ይጠቀሙ።

እንዲሁም User Name በሚለው ቦታ ላይ በምዝገባ ወቅት የጻፉትን የኢሜል አድራሻ (email address ) መጻፍ የይለፍ ቃል (Password): changeme – በማስገባት ስልጠናውን መከታተል የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.