Fana: At a Speed of Life!

የሃራ፣ድሬ ሮቃ፣ ሃሮ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃራ፣ ድሬ ሮቃ፣ሃሮ ወረዳዎችና አካባቢዎቻቸው ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር የወልድያ ተንቀሳቃሽ የሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ በመዘረፍ ምክንያት ለረጅም ጊዜ አገልግሎቱ ተቋርጦባቸው የቆዩ የሃራ፣ድሬ ሮቃ፣ ሃሮ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ከዛሬ ጀምሮ ዳግም የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ጀምረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የወልዲያ ዶሮ ግብር ባለ 230/33/15 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ አካባቢዎቹ ዳግም የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በ33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ የተደረጉት ሀራ፣ ድሬ ሮቃ፣ሃሮ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው ከአንደ ዓመት ከስድስት ወር በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸው ቆይቷል፡፡

ከወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ አገልግሎት ያገኙ የነበሩ በአፋር ክልል በከልዋን ዞን የሚገኙ ወረዳዎች ጭፍራ፣ አውራ እዋና አለሌ ዳግም በጥቂት ቀናት ውስጥ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የወልዲያ ዶሮ ግብር የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም በከፊል አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ የወልዲያ ከተማና አካባቢው ዳግም የ24 ስዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት መጀመራቸው ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.