Fana: At a Speed of Life!

አቡበከር ናስር ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቡበከር ናስር በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጊኒን ከሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች አንዱ የነበረው አቡበከር ናስር ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ ማገገም ባለመቻሉ ነው ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ የሆነው፡፡

በምትኩም የኢትዮጵያ መድኑ አጥቂና በቻን ውድድር የብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ኪቲካ ጀማ ጥሪ የተደረገለት መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና ኮከብ አቡበከር ናስር ክለቡ ማማሎዲ ሰንዳውንስ ከኦርላንዶ ፔሬትስ ጋር ባደረገው ጨዋታ ጉዳት በማስተናገዱ  ለወራት ከጨዋታ ርቆ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.