Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለው የሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል በመጠናቀቅ ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረር ከተማ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ እየተገነባ ያለው የሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

በሐረር ከተማ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል የጋዜጠኞችና የኮሙኒኬሸን ባለሙያዎች ቡድን ዛሬ ጎብኝቷል፡፡

የባህል ማዕከሉ የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት እንዲሁም ስለ ሀገራቸውና ስለ ሐረሪ ክልል ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ለማስተዋወቅ ያስችላል ተብሏል።

ሐረር የመቻቻልና የፍቅር ከተማ መሆኗን በተጨባጭ ለማሳየትና የቱሪዝም ማዕከልነቷን ለማሳደግ የባህል ማዕከሉ ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም የሐረሪ ክልል ቅርስ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለደ አብዶሽ ተናግረዋል፡፡

የባህል ማዕከሉ የወጣቶች ስብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ የሐረሪ እና የኦሮሞን ባህል የሚያንጸባርቁ ጎጆዎች፣ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የስብሰባ አዳራሽን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት መስጫዎችን ያካተተ መሆኑን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.