Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ኩባንያዎች በድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠና በተሽከርካሪ ምርት ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2015 (ኤፍቢ ሲ) ከሩሲያ የላዳ እና ጋዝ ግሩፕ መኪና አምራች ኩባንያዎች የመጡ ተወካዮች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ሽፈራው ሰለሞን ጋር ተወያዩ፡፡

ለተወካዮቹ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንትሁኔታ፣ ስለዘርፉ ማበረታቻዎች እንዲሁም በአፍሪካ ግንባር ቀደም ስለሆነው የድሬዳዋ የነጻ ንግድ ቀጠና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

ኃላፊዎቹ የቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የስራ እንቅስቃሴና የምርት ሂደት ተመልክተዋል፡፡

ኩባንያዎቹ በአውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካና የአፍሪካ ገበያዎች ለጤና ተቋማት፣ ለፀጥታ አካላት፣ ለጭነት አገልግሎት እንዲሁም ለግልና ለህዝብ ትራንስፖርት ዘርፍ የሚውሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡

ተወካዮቹ በተለይም በድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ኢንቨስት በማድረግ የተለያዩ ምዴል ምርቶችን በኢትዮጵያ ገበያ የማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.