Fana: At a Speed of Life!

ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በሞሃመድ ናስር ግብ መምራት ቢችልም ሃብታሙ ታደሰ አስቆጥሮ በአንድ አቻ ውጤት ወደ እረፍት አምርተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ አለልኝ አዘነ በጨዋታ እንዲሁም ያሬድ ባዬ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ አስቆጥረው በሙሉ ሰዓት ውጤት ባህር ዳር ከነማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶች ወደ ዋንጫ ፉክክሩ የተመለሱ ሲሆን ÷ከመሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት  አጥብበዋል፡፡

የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ መርሐ ግብር በሀዋሳ ዩኒቨርሲት ስታዲየም ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከድሬዳዋ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.