Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ዛሬ እንደሚጠናቅ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015 በአምራቹና በፋይናንስ አቅራቢ ተቋማት መካከል የነበረውን የቅንጅት ክፍተት በመፍታት ተቋማቱ ለዘርፉ እድገት ተቀራርበው እንዲሰሩ በማስቻል ረገድ የፈጠረው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ለግል ዘርፉ የተመቸ የፋይናንስ አቅርቦት ሥርዓት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የግብዓት ትስስር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያዊ የፖሊሲ ማዕቀፍ ለኢንዱስትሪ ትስስር በሚል መሪ ሃሳብ̎ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የፓናል ውይይት መድረኮችም መካሄዳቸው ይታወሳል።

ኤክስፖው ኢትዮጵያ በዘርፉ ትልቅ አቅም ያላት መሆኑን ያሳየ ሲሆን÷ ሌሎች ባለኃብቶችንም ወደ ዘርፉ ለመሳብ ጥሩ አጋጣሚ ነው ተብሏል፡፡

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.