Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ እንቅስቃሴን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል የምታካሂደውን የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ለማጠናከር ሀገራቱ በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ የንግድ እንቅስቃሴን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች እየተወያዩ ነው፡፡

በውይይቱ የጅቡቲ ንግድ ሚኒስቴር ዋና ጸሃፊ አሊ ዳውድን ጨምሮ የዓለም ባንክ ተወካይ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ ካሳሁን ጎፌ፥ ኢትዮጵያ በጅቡቲ ወደብ በኩል የምታካሂደውን የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ለማጠናከር ሁለቱ ሀገራት ሊሰሩበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

በመድረኩ በኢትዮጵያና በጀቡቲ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ የቁም እንሰሳት ወጪ ንግድ ለማጠናከር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችመገምገማቸውን አንስተዋል፡፡

ይህም በጅቡቲ ወደብ እና በሚሌ ኳራንታይን አጠቃቀም ዙሪያ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ የቁም እንስሳትን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ገበያ መላክ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚስያስችል ጠቁመዋል፡፡

የቁም እንስሳት ወጪ ንግድን ለማሻሻል የዓለም ባንክ ባደረገው የገንዘብ ድጋፍ “ድራይቭ“ በተሰኘ ፕሮጀክት ታግዞ እየተሰራ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.