Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ቋንቋ ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ቋንቋ ቀን የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።

በዝግጁቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ፔድሮ የሩሲያ ቋንቋ ቀን የቋንቋ እና የባህል ብዝሃነትን በመላው ዓለም ለመገንባት እየተደረገ ያለው ጥረት አካል ነው ብለዋል።

በህዝቦች መካከል መግባባትን እና የእርስ በእርስ ትውውቅን ለመፍጠር ቋንቋ መሰረት ነው ያሉት ዋና ጸሀፊው፥ የሩሲያን ቋንቋ በአፍሪካ ሃገራት ለማስተዋወቅ ኮሚሽኑ የበኩሉን ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ይቭጌኒ ተረኺን በበኩላቸው የዓለም የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት

የሩሲያ የቋንቋ ቀን የሀገሪቱ የዘመናዊው የቋንቋ እና ስነ ፅሁፍ አባት አሌክሳንደር ሰርጌቪች ፑሽኪን የልደት ቀን በፈረንጆቹ ሰኔ 6 ቀን እንዲከበር መወሰኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያም ሆነ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የሩሲያ ቋንቋ ስልጠና በተለያዩ አግባቦች እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሰጠቱ የህዝብ ለህዝብ የባህል እና የቱሪዝም ትስስርን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑ በዝግጁቱ ላይ ተገልጿል።

በዝግጁቱ ላይ በሩሲያ ቋንቋ የተጻፉ ግጥሞች እና ሌሎች የስነ ጽሁፍ ውጤቶች ቀርበዋል።

በወንደሰን አረጋኸኝ እና ፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.