Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሳዶካን ከ28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ሳንዶካን ደበበ ከ28ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድናን አሕመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ሳዶካን ደበበ÷ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፋዊ ስምምነት የቋሚ ኮሚቴዎች ስብሰባ ጎን ለጎን ነው ከዋና ሥራ አስፈጻሚው ጋር የተወያዩት፡፡

ሚኒስትር ዴዔታው በውይይቱ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሕዳር 2016 በዱባይ በሚካሄደው 28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ለመሳተፍ ዝግጅት ጀምራለች፡፡

ኢትዮጵያ በተሳትፎዋ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ጋር በቅርበት እና በመደጋገፍ ለመስራት ያላትን ፍላጎትም ገልጸዋል፡

አቶ አድናን አሕመድ በበኩላቸው ÷28ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ የተሳካ እንዲሆን ኢትዮጵያ ድጋፍ እንድታደርግ ጠይቀዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.