Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የደቡብ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ ÷ በግማሽ ዓመቱ ከመደበኛ ግብር ከፋዮች እና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚጠበቀውን ግብር ለመሰብሰብ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

የታቀደውን እቅድ በስኬት ለማጠናቀቅም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት በቅንጅት መሰራቱን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱም ከ18 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ነው አቶ ይግለጡ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

ገቢው ከ188 ሺህ በላይ ከሆኑ የመደበኛ ግብር ከፋዮች እና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከገቢ አሰባሰብ ጋር ተያይዞ ብልሹ አሰራር ሲፈጽሙ በተገኙ የቢሮው ሰራተኞች ላይ እርምጃ መወሰዱንም አስረድተዋል፡፡

ደረሰኝ የማይከፍሉ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ህጋዊ መስመሩን ተከትለው እንዲሰሩ የተለያዩ ህጋዊ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ሃላፊው አብራርተዋል፡፡

በቀጣይ ዓመት ግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንዲከፍሉ አስፈላጊው ቅስቀሳ እና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.