Fana: At a Speed of Life!

ዴቪድ ሲልቫ ከእግር ኳስ ራሱን አገለለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የመሀል ክፍል ተጫዋች ዴቪድ ሲልቫ በ37 ዓመቱ ከእግር ኳስ ራሱን አግልሏል፡፡

የቀድሞው የማንቸስተር ሲቲ ባለውለታ ዴቪድ ሲልቫ ከከባድ የቁርጭምጭሚት ጉዳት በኋላ ነው ከኢንተርናሽናል እግር ኳስ ራሱን እንዳገለለ ያስታወቀው፡፡

ሲልቫ በፈረንጆቹ 2010 ከስፔኑ ቫሊንሲያ ማንቸስተር ሲቲን የተቀላቀለ ሲሆን÷ ከቡድኑ ጋር አስር ዓመታትን በማሳለፍ አራት የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል፡፡

ሲልቫ በ2020 ማንቸስተር ሲቲን በመልቀቅ ከስፔኑ ሪያል ሶሽዳድ ጋር ሶስት ዓመታትን ቢያሳልፍም÷ በላሊጋው የቅድመ ውድድር ዝግጅት ላይ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት እግር ኳስ ለማቆም መወሰኑ ተገልጿል፡፡

የመሀል ክፍል ጨዋታ አቀጣጣዩ ዴቪድ ሲልቫ ከስፔን ብሄራዊ ቡድን ጋር በ2008 የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግን እንዲሁም በ2010 የዓለም ዋንጫን ማንሳት መቻሉን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.