Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ አሜሪካ ያቀናል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማድረግ በነገው እለት ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የዋሊያዎቹ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ አስመልክቶ የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን  እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ  ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረ ማሪያም  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥዋል፡፡

በመግለጫው የብሔራዊ ቡድኑ  አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም ÷ብሔራዊ ቡድኑ በቆይታው ጠንካራ የልምድ ልውውጥ  የሚያደረግበትና ለተጨዋቾች የመታየት እድል የሚገኝበት መሆኑን ገልጸዋል ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን  በአሜሪካ ቆይታው ሐምሌ 26 ቀን 2015ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ከጉያና  ብሔራዊ ቡድን ፤ሐምሌ 29 ቀን 2015ዓ.ም በሳውዘርን ክረሰንት ስታዲየም ከአትላንታ ሮቨርስ ይጫወታል ።

የፌዴሬሽኑ ዋና ፀኃፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው÷ ከብሔራዊ ቡድኑ የተካተቱ አራት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተጨዋቾች ከአትላንታ ሮቨርስ ጋር በሚደረገው ጨዋታ የመሰለፍ እድል እንደሚያገኙ ተናግረዋል ።

የብሔራዊ ቡድኑ በሁለት ልዑክ ተከፍሎ ወደ ስፍራው የሚያቀና  መሆኑን የጠቆሙት ዋና ፀሃፊው÷የመጀመሪያው ልዑክ ነገ ሲጓዝ ሁለተኛው ልዑክ ከነገ  በስቲያ ወደ ስፍራው ያቀናል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.