Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ዛሬ ጠዋት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአለም ባንክ ፕሬዚዳንት አጃይ ባንጋ ጋር በመሆን በአንደኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ በምርት ስራ ላይ ካሉ ኢንዱስትሪዎች ሁለቱን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ፥ ኢትዮጵያ ለብዙ ሺህዎች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ያስገኙ 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ገንብታ ወደ ስራ አስገብታለች ብለዋል።

የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችንም ተገንብተው በስራ ላይ እንደሚገኙም ነው የገለጹት።

ኢትዮጵያ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር ብቻ ሳትሆን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች መዋእለ ነዋይ ለማፍሰስ ለሚሹ ሁሉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረች እንደሆነም ጠቁመዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ከዚህ ጋር ተያይዞ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎችን ማሳደግ የኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ዋና አካል መሆኑን ገልጿል።

መንግስት በርከት ያለ የሰለጠነ የሰው ኃይልና ለንግድ ምቹ ከባቢን ለመፍጠር በሚያደርገው ጥረት ኢትዮጵያ ወሳኝ የኢንዱስትሪ መዳረሻ መሆኑዋን ታሳቢ አድርጓልም ነው የተባለው።

ከጉብኝቱም ጎን ለጎን ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የአለም ባንክ ፕሬዚዳንቱ ችግኞች ተክለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.