Fana: At a Speed of Life!

አማኑኤል ገብረሚካኤል ፋሲል ከነማን በይፋ ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የመቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል ፋሲል ከነማን በይፋ ተቀላቅሏል፡፡

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የነበረውን ኮንትራት ያጠናቀቀው አጥቂው እስከ 2017 ዓ.ም በሚያቆይ ኮንትራት ለፋሲል ከነማ መፈረሙን ክለቡ አስታውቋል፡፡

አማኑኤ ገብረ ሚካኤል ከዚህ በፊት በዳሽን ቢራ፣ በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን፣ በመቀሌ 70 እንደርታ ፣ በቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቷል።

አማኑኤል ዓጼዎቹን መቀላቀሉን ተከትሎም ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በክለብ እና በብሄራዊ ቡድን አብሮ የመስራት እድል አግኝቷል፡፡

ቀደም ሲል ወሳኙን አጥቂ ጌታነህ ከበደን ማስፈረም የቻሉት ዓጼዎቹ ሌላኛውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ ምኞት ደበበን ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነግሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.