Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት በጉባዔው አባላት በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ዛሬ ጠዋት በአርባ ምንጭ ከተማ በተካሄደው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባዔ የቀረበው ሕገ-መንግስት በ 10 ተቃውሞ፣ በ2 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግስት ይዘት ለጉባዔው አባላት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ነው የጸደቀው፡፡

በህገ መንግስቱ የክልሉ የሥራ ቋንቋ አማርኛ መሆኑ የተቀመጠ ሲሆን ሌሎችንም ቋንቋዎች ለማሳደግ ዕድል የሰጠ መሆኑምተመላክቷል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫ ወላይታ ሶዶ መሆኑ በሕገመንግስቱ የተቀመጠ ሲሆን የተለያዩ ቢሮዎችም በሶዶ፣ በአርባምንጭ፣ በዲላ፣ በጂንካ፣ በሣውላና በኮንሶ ካራት ከተሞች ይኖራሉ።

የክልሉ ሰንደቅዓላማም ከላይ አረንጓዴ፣ ከመሀል ውሃ ሰማያዊ ከታች ቀይ ሆኖ በጥቁር መሥመር ተለያይተው አግድም የሚቀመጥ ሲሆን ከበስተግራ በኩል ከመስቀያው ጠርዝ ከአረንጓዴና ቀይ ቀለም ጫፎች በመነሳት በመሀል ሰማያዊ ቀለም መደብ ላይ በተገናኙ ጥቁር መስመሮች በሚፈጠር ባለሦስት ማዕዘን ቅርፅ ቢጫ ቀለም የተዋቀረ ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።

በማቱሣላ ማቴዎስ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.